መዝሙር 69:36 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የአገልጋዮቹም ዘሮች ይወርሱአታል፤ እርሱን የሚወዱ ሁሉ እዚያ ይኖራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የባሪያዎቹም ዘሮች ይወርሷታል፤ ስሙንም የሚወድዱ በዚያ ይኖራሉ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ጽዮንን ያድናታልና፥ የይሁዳንም ከተሞች ይሠራልና፥ በዚያም ይቀመጣሉ ይወርሱአትማል። |
የአገልጋዮቼን መልእክት አጸናለሁ፤ የነቢያቴንም ትንቢት እንዲፈጸም አደርጋለሁ፤፥ እነርሱም ኢየሩሳሌም፦ ‘የብዙ ሕዝብ መኖሪያ ትሆናለች፤ የይሁዳ ከተሞችም እንደገና ይሠራሉ፤ ፍርስራሾቻቸውም ይታደሳሉ’ ይላሉ።
ልጆቻቸው በወገኖች ዘንድ፥ የልጅ ልጆቻቸውም በሕዝቦች ዘንድ የታወቁ ይሆናሉ። የሚያዩአቸው ሁሉ በእኔ በእግዚአብሔር የተባረኩ ዘሮች መሆናቸውን ያውቃሉ።
የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ! ስሙ፤ እግዚአብሔር በእምነት ሀብታሞች እንዲሆኑና እርሱን ለሚወዱት ተስፋ የሰጣቸውን መንግሥት እንዲወርሱ የዚህን ዓለም ድኾች አልመረጠምን?
ጸያፍ የሆነ ነገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ርኲሰትን የሚያደርግና ውሸት የሚናገር ከቶ ወደ እርስዋ አይገባም፤ ወደ እርስዋ የሚገቡ ስሞቻቸው በበጉ የሕይወት መጽሐፍ የተጻፉ ብቻ ናቸው።