መዝሙር 69:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስድብ ልቤን ስለ ሰበረው ተስፋ ቈረጥኩ፤ የሚያስተዛዝነኝ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንም አልነበረም፤ የሚያጽናናኝ ሰው ፈለግኹ፤ ነገር ግን ማንም አልተገኘም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስድብ ልቤን ጐድቶታል፤ ተስፋዬም ተሟጥጧል፤ አስተዛዛኝ ፈለግሁ፤ አላገኘሁምም፤ አጽናኝም ፈለግሁ፤ አንድም አልነበረም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አንተ ስድቤን እፍረቴንም ነውሬንም ታውቃለህ፥ የሚያስጨንቁኝ ሁሉ በፊትህ ናቸው። |
ዙሪያዬን በተመለከትኩ ጊዜ የሚረዳ ማንም አልነበረም። ደጋፊ ባለመኖሩ ተደነቅሁ፤ ስለዚህ በኀይለኛ ቊጣዬ አማካይነት እኔው ራሴ ድልን አመጣሁ።
ወደ ሦስቱ ደቀ መዛሙርት ተመልሶ በመጣ ጊዜ፥ ተኝተው አገኛቸው፤ ስለዚህ ጴጥሮስን፦ “ስምዖን ሆይ፥ ተኝተሃልን? አንዲት ሰዓት እንኳ ልትነቃ አልቻልክምን?” አለው።
ቀጥሎም ኢየሱስ እንዲህ አለ፦ “እነሆ! ነፍሴ ተጨንቃለች፤ ምን ልበል? ‘አባት ሆይ! ከዚህች ሰዓት አድነኝ ልበልን?’ ይህን እንዳልል ግን እኔ የመጣሁት ለዚህች የመከራ ሰዓት ነው።
ይሁን እንጂ እያንዳንዳችሁ በየበኩላችሁ የምትበታተኑበትና እኔን ብቻዬን የምትተዉበት ሰዓት ይመጣል፤ ሰዓቱም አሁን ደርሶአል፤ ነገር ግን አብ ከእኔ ጋር ስለ ሆነ ብቻዬን አይደለሁም።