መዝሙር 68:7 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አምላክ ሆይ! ሕዝብህን በመራህ ጊዜ፥ በበረሓም አብረሃቸው በተጓዝህ ጊዜ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ በሕዝብህ ፊት በወጣህ ጊዜ፣ በምድረ በዳም በተጓዝህ ጊዜ፣ ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እግዚአብሔር ብቸኞችን በቤት ያሳድራቸዋል፥ እስረኞችንም በኃይሉ ያወጣቸዋል፥ ዓመፀኞች ግን በምድረ በዳ ይኖራሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስለ አንተ ስድብን ታግሻለሁና፥ እፍረትም ፊቴን ሸፍኖኛልና። |
ለተጨቈኑት መልካም ዜናን አበሥር ዘንድ፥ ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩት ነጻነትን፥ ለታሰሩት መፈታትን ለማወጅ እግዚአብሔር ቀብቶ ስለ ላከኝ፥ የጌታ እግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው።
መንገዱን በርግዶ በሚከፍትላቸው መሪ አማካይነት በተከፈተው ሰፊ በር ተግተልትለው ይወጣሉ፤ እግዚአብሔርም ንጉሣቸው በፊታቸው እየሄደ ይመራቸዋል።
ወይስ በፈተና፥ በተአምራትና በድንቅ ነገሮች፥ በጦርነት፥ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ፥ በሚያስፈራ ኀይል፥ በዐይናችሁ እያያችሁት እግዚአብሔር አምላካችሁ እናንተን ከግብጽ ምድር እንዳወጣችሁ ያለ አንድን ሕዝብ ከሌላ ሕዝብ መካከል ወስዶ የራሱ ሕዝብ ለማድረግ የሞከረ ሌላ አምላክ አለን?
ዲቦራም ባራቅን “እግዚአብሔር አንተን በሲሣራ ላይ ድልን እንድትቀዳጅ የሚያደርግበት ቀን ዛሬ ስለ ሆነ ተነሥ! እነሆ! እግዚአብሔር ይመራሃል” አለችው፤ ባራቅም ዐሥር ሺህ ወታደሮች ተከትለውት ከታቦር ተራራ ወረደ።
እግዚአብሔር ሆይ! ከኤዶም ተራራ በተነሣህ ጊዜ፥ በኤዶምም ምድር ላይ በተራመድህ ጊዜ ምድር ተንቀጠቀጠች፤ ሰማያት ዝናብን አዘነቡ፤ አዎ! ውሃ ከደመናዎች ወደታች ጐረፈ።