“ሸክማችንን በየቀኑ የሚያቀልልንና እኛን የሚያድን እግዚአብሔር አምላክ የተመሰገነ ይሁን።
ሸክማችንን በየዕለቱ የሚሸከምልን፣ አዳኝ አምላካችን፣ ጌታ ይባረክ። ሴላ
ወደ ላይ ዓረግህ፥ ምርኮን ማረክህ፥ ስጦታንም ከሰዎች ወሰድህ፥ ከዓመፀኞችም ጭምር፥ በዚያም ጌታ ያድር ዘንድ።
አንተ ስድቤን፥ እፍረቴንም፥ ነውሬንም ታውቃለህ፤ በሚያስጨንቁኝ ሁሉ ፊት።
አምላክ ሆይ! ሐሳብህ እጅግ የከበረና የሰፋ ስለ ሆነ እኔ ልረዳው አልችልም።
አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፤ ከመከራ ትጠብቀኛለህ፤ ስላዳንከኝ በከፍተኛ ድምፅ በደስታ እዘምራለሁ።
ችግርህን ሁሉ ለእግዚአብሔር አቅርብ፤ እርሱም በእንክብካቤ ይጠብቅሃል፤ እግዚአብሔር ደጋግ ሰዎችን ከቶ ለችግር አሳልፎ አይሰጣቸውም።
ጸሎታችንን ሰምተህ ድልን ታጐናጽፈናለህ፤ እኛንም ለማዳን ብዙ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ፤ ሩቅ ከሆነው ባሕር ማዶ ያሉት ሳይቀሩ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይታመናሉ።
አርጅታችሁ ጠጒራችሁ እስከሚሸብትበት ጊዜ ድረስ፥ የምጠብቃችሁ እኔ ነኝ፤ ፈጥሬአችኋለሁ፤ እንከባከባችኋለሁም፤ እረዳችኋለሁ፤ ከክፉ ነገርም እጠብቃችኋለሁ።
እነርሱ በየማለዳው ይታደሳሉ፤ ስለዚህ የአንተ ታማኝነት ታላቅ ነው።
በሰማይ ባለው መንፈሳዊ በረከት ሁሉ በክርስቶስ የባረከን የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ አባት እግዚአብሔር ይመስገን።