አምላክ ሆይ! ሕዝቦች ያመስግኑህ፤ ሕዝቦች ሁሉ ያመስግኑህ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰዎች ያመስግኑህ፤ ሰዎች ሁሉ ምስጋና ያቅርቡልህ።
ለአሕዛብ በቅን ትፈርድላቸዋለህና፥ አሕዛብንም በምድር ላይ ትመራለህና አሕዛብ ደስ ይበላቸው ሐሤትም ያድርጉ።
እግዚአብሔር በቅዱስ ቦታው ለድሃ አደጎች አባት፥ ለባልቴቶችም ዳኛ ነው።
አምላክ ሆይ፥ ሕዝቦች ያመስግኑህ፤ ሕዝቦች ሁሉ ያመስግኑህ።
እግዚአብሔር ለተጨቈኑት መጠጊያ ነው፤ በመከራ ጊዜም መከላከያ አምባ ነው።
ከእኛ ጋር አብረህ ብትሄድ እግዚአብሔር የሚያደርግልንን መልካም ነገር ሁሉ ለአንተም እናካፍልሃለን።”