መዝሙር 65:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መስኮች የብዙ በጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤ ሸለቆዎች በሰብል ይሸፈናሉ፤ ሁሉም ደስ ብሎአቸው፥ በእልልታ ይዘምራሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሜዳዎች መንጋ በመንጋ ሆኑ፤ ሸለቆችም በእህል ተሸፈኑ፤ እልል ይላሉ፤ ይዘምራሉም። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድረ በዳ መስኮች ይረካሉ፥ ኮረብቶችም በደስታ ይታጠቃሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መባዬን ይዤ ወደ ቤትህ እገባለሁ፤ |
በምድሩ ላይ በቂ እህል ይኑር፤ ተራራዎች በሰብል ይሸፈኑ፤ እንደ ሊባኖስ ተራራዎችም ፍሬያማ ይሁኑ፤ የእህሉም ነዶ እንደ ሣር የበዛ ይሁን።
ዘር በምትዘሩበት ጊዜ ቡቃያችሁን ለማሳደግና ብዙ መከር እንድታገኙ ለማድረግ እግዚአብሔር ዝናብን ይልክላችኋል፤ ከብቶቻችሁም ብዙ የመሰማሪያ ቦታ ያገኛሉ።
እግዚአብሔር የታደጋቸው ሰዎች ተመልሰው ይመጣሉ፤ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይገባሉ፤ ዘወትር የደስታን ዘውድ ይቀዳጃሉ፤ ተድላና ደስታንም ያገኛሉ፤ ማዘንና መቃተት ከእነርሱ ይርቃል።
ሰማያት ሆይ! እግዚአብሔር ሕዝቡን እስራኤልን በማዳን ክብሩን ገልጦአልና በደስታ ዘምሩ፤ ምድርም ከታች እልል በዪ፤ ተራራዎች፥ ጫካዎችና በውስጣቸው የምትገኙ ዛፎች ሁሉ የደስታ ድምፅ እያሰማችሁ ፈንድቁ።
“እናንተም ከባቢሎን በደስታ ወጥታችሁ፥ በሰላም ወደ ሀገራችሁ እንድትመለሱ ትደረጋላችሁ፤ ተራራዎችና ኰረብቶች በፊታችሁ በመዘመር ይፈነድቃሉ፤ የሜዳ ዛፎችም በእጆቻቸው ያጨበጭባሉ።
ደስታና ሐሴት ለምለም ከሆነችው ከሞአብ ምድር ተወስደዋል፤ ከወይን መጭመቂያዎች ሁሉ የወይን ጠጅ እንዳይፈስስ አድርጌአለሁ፤ የደስታ ድምፅ እያሰማ የሚጨምቅ የለም፤ ድምፅ የሚሰማ ቢሆንም የሚሰማው ድምፅ ግን የደስታ ድምፅ አይደለም።
ይሁን እንጂ እርሱ እንዴት ያለ ቸር አምላክ መሆኑን የሚመሰክር መልካም ሥራ ማድረጉን አላቋረጠም፤ ከሰማይ ዝናብን አዘነበላችሁ፤ የመከር ወራትንም ሰጣችሁ፤ በምግብና በደስታ ልባችሁን አረካ።”