አምላክ ሆይ! አንተ ብርታቴ ነህ፤ አንተ መጠጊያዬ ነህ፤ ዘለዓለማዊ ፍቅርህንም ታሳየኛለህ፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ።
ብርታቴ ሆይ፤ ውዳሴ አቀርብልሃለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ መጠጊያዬ፣ የምትወድደኝም አምላኬ ነህና።
እኔ ግን ለኃይልህ እቀኛለሁ፥ በምሕረትህም ማልዶ ደስ ይለኛል፥ በመከራዬ ቀን መጠጊያዬና አምባዬ ሆነኸኛልና።
እግዚአብሔር ሆይ! ኀይል የምትሰጠኝ አንተ ስለ ሆንክ፥ እወድሃለሁ።
እግዚአብሔር መጠጊያችንና ኀይላችን ነው፤ ችግር በሚደርስብን ጊዜ ሁሉ ረዳታችን ነው።
ስለዚህ ምድር ብትናወጥ፥ ተራራዎች ወደ ጥልቅ ባሕር ቢወድቁ፥
ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ከሰማያት በላይ ነው፤ ታማኝነትህም ወደ ጠፈር ይደርሳል።
አምላክ ሆይ! ከሰማያት ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም ከምድር ሁሉ በላይ ይሁን።
መዝሙር ለመዘመር ተነሡ፤ ከበሮም ምቱ፤ በበገናና በመሰንቆ ደስ የሚያሰኝ ዜማ አሰሙ።