እየሄደ ሟምቶ እንደሚያልቅ ቀንድ አውጣና ሞቶ እንደ ተወለደና ብርሃንን ከቶ እንዳላየ ጭንጋፍ ይሁኑ።
ሲሄድ እንደሚቀልጥ ቀንድ አውጣ ይሁኑ፤ ፀሓይን እንደማያይ ጭንጋፍ ይሁኑ።
እንደሚፈስስ ውኃ ይጥፉ፥ ቀስትን ሲገትሩ ፍላጻው ይጣመም።
የምትሰማቸው አንተ ግን አቤቱ፥ ትሥቅባቸዋለህ፥ አሕዛቡንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ፥
ሳልፈጠር በቀረሁ፥ ከማሕፀንም በቀጥታ ወደ መቃብር ብወሰድ ኖሮ በተሻለኝ ነበር።
ወይስ ለምን በመሬት ውስጥ እንደ ተቀበረ ጭንጋፍ የቀንን ብርሃን ፈጽሞ እንዳላየ ሕፃን አልሆንኩም?
እንግዲህ፥ አንድ ሰው መቶ ልጆች ቢወልድ፥ ረጅም ዕድሜ አግኝቶ ብዙ ዘመን በሕይወት ቢኖርም፥ እንዲደሰትበት ከሚያስፈልገው ነገር ሁሉ ድርሻውን ሳያገኝ ቀርቶ በመጨረሻም በክብር ለመቀበር ሳይበቃ ቢቀር፥ እኔ ስለ እርሱ አዝናለሁ፤ ከእንደዚህ ያለውም ሰው ይልቅ በእናቱ ማሕፀን ሞቶ የተወለደ ጭንጋፍ ይሻላል አልኩ።
ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።”
የሰው ሀብት እንደ ሣር አበባ ስለሚረግፍ በኑሮው ከፍ ያለ ወንድም እግዚአብሔር በኑሮው ዝቅ ቢያደርገውም ደስ ይበለው፤