ልቤ ጽኑ ነው፤ አምላክ ሆይ! ልቤ ጽኑ ነው፤ በመልካም ቃና እዘምርልሃለሁ!
እግዚአብሔር ሆይ፤ ልቤ ጽኑ ነው፤ ልቤ ጽኑ ነው፤ እቀኛለሁ፤ እዘምራለሁ።
ለእግሮቼ ወጥመድን አዘጋጁ፥ ነፍሴንም አጐበጡአት፥ ጉድጓድ በፊቴ ቈፈሩ፥ በእርሱም ወደቁ።
እንደሚፈስስ ውኃ ይቀልጣሉ፤ እስከሚያደክማቸው ድረስ ፍላጻቹን ይገትራል።
እምነቱ ጽኑ ስለ ሆነና በእግዚአብሔርም ስለሚተማመን፥ ክፉ ወሬ አያስደነግጠውም።
ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ እኔ ግን ከትእዛዞችህ ፈቀቅ አላልኩም።
እግዚአብሔርን “አንተ አምላኬ ነህ” እለዋለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ! ምሕረትህን ለማግኘት ስጸልይ ስማኝ!
ከዘረጉብኝ ወጥመድ ጠብቀኝ፤ ከክፉ አድራጊዎችም መሰናክል አድነኝ።
የእግዚአብሔርን ርዳታ ፈለግኹ እርሱም ሰማኝ፤ ከምፈራውም ነገር ሁሉ አዳነኝ።
ያለ ምክንያት ወጥመድ በድብቅ ዘርግተውብኛል፤ እኔንም ለመያዝ ጒድጓድ ቆፍረዋል።
የሚያመጡት ችግር በራሳቸው ላይ ይደርሳል፤ በክፉ ድርጊታቸውም ዐናታቸው ይፈጠፈጣል።
ስለዚህ በምሥራቅ ያሉት ለእግዚአብሔር ክብር ይሰጣሉ፤ በደሴቶች ያሉ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ከፍ ከፍ ያደርጋሉ።
በዚህ ብቻ ሳይሆን መከራ ትዕግሥትን እንደሚያስገኝልን ስለምናውቅ በመከራችንም እንመካለን።
በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስለ ሁሉ ነገር እግዚአብሔር አብን ዘወትር አመስግኑ።