መዝሙር 52:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የእግዚአብሔር ሰዎችም ይህን አይተው ይፈራሉ፤ እንዲህ እያሉ ይሳለቃሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጻድቃን ይህን አይተው ይፈራሉ፤ እንዲህ እያሉም ይሥቁበታል፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሚያጠፋ ቃልን ሁሉ፥ የሽንገላ ምላስን ወደድህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መድኀኒትን ከጽዮን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል እስራኤልም ሐሤትን ያደርጋል። |
ስለ እርሱም እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፥ ‘ሰናክሬም ሆይ! የኢየሩሳሌም ሕዝብ አንተን በመናቅ ያፌዙብሃል፤ በምትሸሽበትም ጊዜ ከበስተኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።
ጌታ ሆይ! አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ፤ የእውነት ፍርድህ ስለ ተገለጠ፥ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”
ሰማይ ሆይ! በእርስዋ ደስ ይበልህ! እግዚአብሔር ስለ እናንተ በእርስዋ ላይ ስለ ፈረደባት እናንተ ቅዱሳንና ሐዋርያት ነቢያትም ደስ ይበላችሁ!