ራሳቸውንም ከባዕዳን ሕዝቦች ሁሉ ለዩ፤ ከዚህም በኋላ ሁሉም ተነሥተው በመቆም፥ እነርሱና የቀድሞ አባቶቻቸው የሠሩትን ኃጢአት ሁሉ ተናዘዙ።
መዝሙር 51:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ስሕተቴን ዐውቃለሁ፤ የኃጢአቴንም ብዛት ዘወትር እገነዘባለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ መተላለፌን ዐውቃለሁና፤ ኀጢአቴም ዘወትር በፊቴ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፥ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመልካም ይልቅ ክፋትን፥ ጽድቅንም ከመናገር ይልቅ ዐመፃን ወደድህ። |
ራሳቸውንም ከባዕዳን ሕዝቦች ሁሉ ለዩ፤ ከዚህም በኋላ ሁሉም ተነሥተው በመቆም፥ እነርሱና የቀድሞ አባቶቻቸው የሠሩትን ኃጢአት ሁሉ ተናዘዙ።
እርሱም በሰዎች ፊት እንዲህ ብሎ ይዘምራል፤ ‘እኔ ኃጢአት ሠርቻለሁ፤ የቀናውንም ነገር አጣምሜአለሁ፤ እግዚአብሔር ግን በደሌን አልቈጠረብኝም።
በዚያን ጊዜ ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፤ በደሌንም ከአንተ አልሰወርኩም፤ ኃጢአቴን ሁሉ ለአንተ ለመናዘዝ ወሰንኩ፤ አንተም ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር አልክልኝ።
ከቊጥር በላይ የሆኑ ችግሮች ያስጨንቁኛል! በደሎቼ ስለ በዙ ማየት አልችልም፤ እነርሱም በቊጥር ከራስ ጠጒሮቼ ይበልጣሉ፤ ስለዚህ ልቤም እየከዳኝ ነው።
ይህም ሁሉ ሆኖ ኃጢአታችሁን ይቅር የምል አምላክ እኔ ነኝ፤ ይህንንም የማደርገው ስለ እናንተ ሳይሆን ስለ እኔነቴ ነው፤ ስለዚህ ኃጢአታችሁን አልቈጥርባችሁም።
እኛና የቀድሞ አባቶቻችን በመደጋገም ኃጢአት በመሥራት እግዚአብሔር አምላካችንን አሳዝነናል፤ ትእዛዞቹንም አልፈጸምንም፤ ስለዚህ በዕፍረት ልንወድቅና ውርደትም እንደ ልብስ ሊሸፍነን ይገባል።”