መዝሙር 50:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኰርማዎችን ሥጋ እበላለሁን? ወይስ የፍየሎችን ደም እጠጣለሁን? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለመሆኑ፣ እኔ የኰርማ ሥጋ እበላለሁን? የፍየልንስ ደም እጠጣለሁን? መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የፍሪዳውን ሥጋ እበላለሁን? የፍየሉንስ ደም እጠጣለሁን? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) መንገድህን ለኃጥኣን አስተምራቸው ዘንድ፥ ዝንጉዎችም ወደ አንተ ይመለሱ ዘንድ። |
አንድ ሰው ይህን መባ ለእግዚአብሔር የምስጋና መሥዋዕት አድርጎ ለማቅረብ ቢፈልግ፥ ከሚሠዋው እንስሳ ጋር እርሾ ያልነካው በዘይት ተለውሶ የተጋገረ ዳቦ፥ እርሾ ያልገባበት በስሱ ተጋግሮ ዘይት የተቀባ ዳቦ፥ በላመ ዱቄት በዘይት ተለውሶ የተጋገረ ዳቦ ያቅርብ።
እንግዲህ ወንድሞቼ ሆይ! እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ፥ ሕያውና የተቀደሰ መሥዋዕት አድርጋችሁ ሁለንተናችሁን እንድታቀርቡ በመሐሪው በእግዚአብሔር ስም እለምናችኋለሁ፤ ይህም ማቅረብ የሚገባችሁ ቅንነት ያለው እውነተኛ የእግዚአብሔር አገልግሎት ነው።