ከረግረግ ቦታና ጭቃማ ከሆነው ከሚያዳልጥ ጒድጓድ አወጣኝ፤ እግሮቼን በአለት ድንጋይ ላይ አድርጎ የምቆምበትን ጠንካራ ቦታ ሰጠኝ።
ከሚውጥ ጕድጓድ፣ ከሚያዘቅጥ ማጥ አወጣኝ፤ እግሮቼን በዐለት ላይ አቆመ፤ አካሄዴንም አጸና።
በትዕግሥት ጌታን ደጅ ጠናሁት፥ እርሱም ዘንበል አለልኝ ጩኸቴንም ሰማኝ።
እግዚአብሔር ይጠብቀዋል፥ ሕያውም ያደርገዋል፥ በምድር ላይም ያስመሰግነዋል፥ በጠላቶቹ እጅ አሳልፎ አይሰጠውም።
የሞት አደጋ ዙሪያዬን ከበበኝ፤ የመቃብር አስፈሪ ሁኔታ አሠቀቀኝ፤ በችግርና በሐዘን ተሸነፍኩ።
በተስፋ ቃልህ መሠረት አካሄዴን አስተካክል፤ ስሕተትም እንዲሠለጥንብኝ አታድርግ።
ጠላቴ በማሳደድ ተከታተለኝ፤ በጨለማ ውስጥም አስሮ አጐሳቈለኝ፤ ከብዙ ዘመናት በፊት እንደ ሞቱ ሰዎች ሆኜአለሁ።
ዘወትር በመንገድህ ተራመድኩ፤ ከመንገድህም ወጥቼ አልባዘንኩም።
መረማመጃዬን አሰፋህ፤ እግሮቼም አልተንሸራተቱም።
እግዚአብሔር ስለ ተቈጣ ምድር ተናወጠች፤ ተንቀጠቀጠችም፤ የተራሮች መሠረቶች ተናጉ፤ ተነቃነቁም።
በችግር ቀን በጥላው ሥር ይደብቀኛል፤ በመቅደሱ ውስጥ ይሰውረኛል፤ በአለትም ላይ ከፍ አድርጎ ይጠብቀኛል።
እግዚአብሔር በሰው አካሄድ ከተደሰተ የእርምጃውን ትክክለኛነት ያረጋግጥለታል።
ተስፋ ቈርጬ ሳለ ከሩቅ አገር ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ ከእኔ በላይ ወደ አለው ከፍተኛ አምባ ምራኝ።
መቆሚያ ስፍራ ስለ አጣሁ በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ለመስረግ ተቃርቤአለሁ፤ በጥልቅ ውሃ ውስጥ እገኛለሁ፤ ውሃ ሙላት ሊያሰጥመኝ ተቃርቦአል።
በብዙ ችግርና መከራ እንድሠቃይ አድርገኸኛል፤ ሆኖም እንደገና ከመሬቱ ጥልቅ ጒድጓድ አውጥተህ አዲስ ሕይወትን ትሰጠኛለህ።
ለእኔ የምታሳየው ዘለዓለማዊው ፍቅርህ እንዴት ታላቅ ነው! ወደ ሲኦል ጥልቀት ከመውረድ አዳንከኝ።
እግዚአብሔር ነገሥታትን በአንድነት ሰብስቦ በምድር ውስጥ ባለ እስር ቤት ውስጥ እንዳሉ እስረኞች እንዲኖሩ ያደርጋል፤ ከብዙ ቀኖችም በኋላ ይቀጣቸዋል።
“በመሥዋዕት ደም ከአንቺ ጋር ቃል ኪዳን ስለ ገባሁ፥ ውሃ ከማይገኝበት ጒድጓድ እስረኞችሽን ነጻ አወጣለሁ።
ክፉዎችን ወደ እቶን እሳትም ይጥሉአቸዋል፤ በዚያ ለቅሶና ጥርስ ማፋጨት ይሆናል።”
እግዚአብሔር ግን የሞትን ኀይል አስወግዶ ከሞት አስነሣው፤ ስለዚህም ሞት ይዞ ሊያስቀረው አልቻለም።