እንዲረዳኝ በትዕግሥት ጌታን ተጠባበቅሁት። ወደ እኔም መለስ ብሎ ጸሎቴን ሰማ።
እግዚአብሔርን ደጅ ጠናሁት፤ እርሱም ዘንበል አለልኝ፤ ጩኸቴንም ሰማ።
ለመዘምራን አለቃ፥ የዳዊት መዝሙር።
ለድሃና ለምስኪን የሚያስብ ብፁዕ ነው፤ እግዚአብሔር ከክፉ ቀን ያድነዋል።
እርሱን በምጠራው ጊዜ ሁሉ ስለሚሰማኝ፥ በዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጮኻለሁ።
እግዚአብሔር ሆይ! ልመናዬን ስማ! ምሕረትህን ፈልጌ ስጮኽም አድምጠኝ!
እግዚአብሔር ወደ ጻድቃን ይመለከታል፤ ጸሎታቸውንም ያደምጣል።
በትዕግሥት ጸንተህ እግዚአብሔር የሚያደርገውን ለማየት ተጠባበቅ፤ ሌሎች ሰዎች ክፉ ሐሳባቸው ቢሳካላቸው አትበሳጭ።
አምላክ ሆይ! እባክህ አድምጠኝ፤ የእኛን ችግርና በስምህ የምትጠራውን ከተማ ጥፋት ተመልከት፤ ወደ አንተ የምንጸልየው የአንተን ምሕረት በመተማመን እንጂ በእኛ መልካም ሥራ በመመካት አይደለም።