እግዚአብሔር ሆይ! በአንተ እተማመናለሁ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ሆይ! አንተም መልስ ትሰጠኛለህ።
እግዚአብሔር ሆይ፤ በተስፋ እጠብቅሃለሁ፤ ጌታ አምላኬ ሆይ፤ አንተ መልስ ትሰጠኛለህ።
እንደማይሰማ ሰው በአፉም ተግሣጽ እንደሌለው ሰው ሆንሁ።
በጠራሁህ ጊዜ ሰማኸኝ፤ በብርታትህም አበረታኸኝ።
አምላክ ሆይ! ልመናዬን ስለምትሰማ፥ ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፤ ቃሌንም ስማ።
እግዚአብሔር ሆይ! ታዲያ፥ እኔ ተስፋዬን በአንተ ላይ ከማድረግ በቀር ሌላ ምን እጠብቃለሁ?
“እርሱ ግፍና ችግር ደረሰበት፤ ይሁን እንጂ ምንም አልተናገረም፤ ለመታረድ እንደሚወሰድ ጠቦትና በሸላቾቹ ፊት ጸጥ እንደሚል በግ ዝም አለ እንጂ ምንም አልተናገረም።