እኔ ግን ሊሰማ እንደማይችል ደንቆሮ፥ ለመናገር እንደማይችል ድዳ ሰው ነኝ።
እኔ ግን እንደማይሰማ ደንቈሮ፣ አፉንም መክፈት እንደማይችል ዲዳ ሆንሁ።
ነፍሴንም የሚሹአት በረቱብኝ፥ መከራዬንም የሚፈልጉ ከንቱን ተናገሩ፥ ሁልጊዜም በሽንገላ ይመክራሉ።
ወደማልመለስበት ሳልሄድ ዐርፍ ዘንድ ተወኝ።
ክፉዎች ወጥመድ ዘረጉብኝ፤ እኔ ግን ከትእዛዞችህ ፈቀቅ አላልኩም።
አንድ ቃል እንኳ ሳልናገር ዝም አልኩ፤ መልካም ስለ ሆነ ነገር እንኳ አልተናገርኩም፤ ነገር ግን ሥቃዬ ከበፊት ይልቅ እየባሰ ሄደ።
ይህ ሁሉ እንዲደርስብኝ ያደረግኸው አንተ ስለ ሆንክ ዝም እላለሁ፤ አንድ ቃል እንኳ አልናገርም።
“እርሱ ግፍና ችግር ደረሰበት፤ ይሁን እንጂ ምንም አልተናገረም፤ ለመታረድ እንደሚወሰድ ጠቦትና በሸላቾቹ ፊት ጸጥ እንደሚል በግ ዝም አለ እንጂ ምንም አልተናገረም።
ሲሰድቡት መልሶ አልተሳደበም፤ መከራን ሲቀበል በጽድቅ ለሚፈርደው አምላክ ራሱን ዐደራ ሰጠ እንጂ አልዛተም።