ልቤ በፍጥነት ይመታል፤ ኀይሌም ደክሞአል፤ ዐይኖቼም ብርሃን አጥተዋል።
ልቤ በኀይል ይመታል፤ ጕልበት ከድቶኛል፤ የዐይኔም ብርሃን ጠፍቷል።
አቤቱ፥ ፈቃዴ ሁሉ በፊትህ ነው፥ ጭንቀቴም ከአንተ አይሰወርም።
መቅሠፍትህን ከእኔ አርቅ፥ ከእጅህ ብርታት የተነሣ አልቄአለሁና።
አዳኝነትህንና እውነተኛ ቃል ኪዳንህን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ደከሙ።
ሕይወቴ በሐዘን ዕድሜዬም በመቃተት አለቀ፤ በችግሬ ምክንያት ኀይል አጣሁ፤ አጥንቶቼም ደከሙ።
አምላክ ሆይ! ዋላ የምንጭ ውሃ ለማግኘት እንደሚናፍቅ እኔም አንተን ለማየት እናፍቃለሁ።
ከጠላቶቼ ተቃውሞ የተነሣ በጣም በማልቀሴ ዐይኖቼ ፈዘዋል፤ ማየትም ተስኖኛል።
ከመጮኼ ብዛት የተነሣ ደከምኩ፤ ጒሮሮዬም ቈሰለ፤ አምላኬን በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ።
ሐዘኔ ከመብዛቱ የተነሣ ዐይኖቼ ደከሙ፤ እግዚአብሔር ሆይ! በየቀኑ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ እጆቼንም ለጸሎት ወደ አንተ እዘረጋለሁ።
ራሴን ያዞረኛል፤ ከፍርሃት የተነሣም እንቀጠቀጣለሁ፤ ቀኑ ቶሎ እንዲመሽልኝ ተመኘሁ፤ ተስፋ ያደረግኹት ጭላንጭል አስደንጋጭ ሆነብኝ፦
ሕዝቤ ስለ ተፈጀ፥ ሕፃናት በከተማይቱ መንገዶች ላይ ስለሚዝለፈለፉ፥ ዐይኖቼ በለቅሶ ደከሙ፤ አንጀቴ ተንሰፈሰፈ፤ ተስፋም ቈረጥሁ።