La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 37:24 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር በእጁ ስለሚደግፈው ቢደናቀፍም አይወድቅም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ቢሰናከልም አይወድቅም፣ እግዚአብሔር በእጁ ደግፎ ይይዘዋልና።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ቢወድቅም አይጣልም፥ ጌታ እጁን ይዞ ይደግፈዋልና።

Ver Capítulo



መዝሙር 37:24
13 Referencias Cruzadas  

የሚንገዳገዱትን ይደግፋል፤ የወደቁትንም ያነሣቸዋል።


ትሑታንን ከፍ ከፍ ያደርጋል፤ ክፉ አድራጊዎችን ግን በምድር ላይ ጥሎ ያዋርዳቸዋል።


የክፉዎች ኀይል ይሰበራል ጻድቃንን ግን እግዚአብሔር ያበረታቸዋል።


ከረግረግ ቦታና ጭቃማ ከሆነው ከሚያዳልጥ ጒድጓድ አወጣኝ፤ እግሮቼን በአለት ድንጋይ ላይ አድርጎ የምቆምበትን ጠንካራ ቦታ ሰጠኝ።


እግሮችህ ድንጋይ አደናቅፎአቸው እንዳይጐዱ መላእክቱ በእጆቻቸው ይደግፉሃል።


“ለመውደቅ ተቃርቤአለሁ” ባልኩ ጊዜ እግዚአብሔር ሆይ! ዘለዓለማዊ ፍቅርህ ደግፎ አቆመኝ።


ጻድቅ ሰው ሰባት ጊዜ ቢወድቅ እንኳ እንደ ገና ይነሣል፤ ዐመፀኞች ግን ጥፋት ይደርስባቸዋል።


ስምዖን ከባረካቸው በኋላ በተለይ የሕፃኑን እናት ማርያምን እንዲህ አላት፦ “እነሆ! ይህ ሕፃን በእስራኤል ውስጥ ለብዙዎቹ የመጥፋት፥ ለብዙዎቹ ግን የመዳን ምክንያት ይሆናል፤ እርሱም ብዙዎች የማይቀበሉት ምልክት ይሆናል።