መዝሙር 36:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ክፉ ሰው ክፋቱ ስለሚያቈላምጠው ኃጢአቱን ለማየትም ሆነ ለመጥላት አይፈልግም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በደሉ ግልጽ ወጥቶ እንዳይጠላ፣ ራሱን በራሱ እጅግ ይሸነግላልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኃጢአተኛ በራሱ የሚያስት ነገርን ይናገራል፥ የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዐይኖቹ ፊት የለም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንደ ሣር ፈጥነው ይደርቃሉና፥ እንደ ለመለመ ቅጠልም ፈጥነው ይረግፋሉና። |
ታዲያ ‘ራሴን ከቶ አላረክስም፤ ለበዓልም ከቶ አልሰግድም’ ብለሽ ለማስተባበል እንዴት ትችያለሽ? በሸለቆ ውስጥ ኃጢአት በመሥራት ያደረግሽውን ርኲሰት እስቲ ተመልከቺ፤ በፍትወት እንደ ተቃጠለች የበረሓ ግመል፥ ወዲያና ወዲህ ትባዝኚአለሽ።
ታዲያ፥ እኛ አይሁድ ከአሕዛብ እንበልጣለን ማለት ነውን? ከቶ አይደለም! ሰዎች ሁሉ አይሁድም ሆኑ አሕዛብ ኃጢአተኞች መሆናቸውን ቀደም ብዬ አስረድቻለሁ።
እንደዚህ ያለው ሰው የዚህን ርግማን ቃላት ሰምቶ ምንም እንኳ በራሴ መንገድ ብቀጥል እኔ እድናለሁ ብሎ በልቡ ቢያስብ በደጎችና በክፉዎች ሰዎች ላይ ጥፋትን ያመጣል።