ጋሻና ጥሩር ያዝ፤ መጥተህም እርዳኝ።
ትልቁንና ትንሹን ጋሻ ያዝ፤ እኔንም ለመርዳት ተነሥ።
ጥሩርና ጋሻ ያዝ፥ እኔንም ለመርዳት ተነሥ።
በአንደበቱ ሸንግሎአልና፤ ኀጢአቱ ባገኘችው ጊዜ ይጠላታል።
በጥበቃው ሥር ያደርግሃል። እርሱ ስለሚንከባከብህ በሰላም ትኖራለህ፤ የእርሱ ታማኝነት እንደ ጋሻ ወይም እንደ ከተማ ቅጽር ይሆንልሃል።
እግዚአብሔር ብርቱ ጦረኛ ነው፤ ስሙም እግዚአብሔር ነው።
እነርሱም በምድር ዳርቻ ከሚገኙ ከሩቅ አገሮች የመጡ ናቸው፤ እግዚአብሔር አገሪቱን በሞላ ለማጥፋት የቊጣ መሣሪያ የሆነ ሠራዊቱን አሰልፎአል።
እግዚአብሔር እንደ ጀግና ወታደር ይወጣል፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ ጦርነትን ያውጃል፤ በጠላቶቹም ላይ ድልን ይጐናጸፋል።