መዝሙር 26:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ፈትነኝ፤ ምኞቴንና ሐሳቤንም መርምር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ፈትነኝ፤ መርምረኝም፤ ልቤንና ውስጤን መርምር፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ፈትነኝ መርምረኝም፥ ኩላሊቴንና ልቤን መርምር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ክፉዎች ሥጋዬን ይበሉ ዘንድ በቀረቡ ጊዜ፥ የሚያሠቃዩኝ እነዚያ ጠላቶቼ ደከሙ፥ ወደቁም። |
የሠራዊት አምላክ ሆይ! ጻድቅን ፈትነህ ታረጋግጣለህ፤ የልብንም ጥልቅ ሐሳብ ትመረምራለህ፤ አቤቱታዬን ለአንተ አቅርቤአለሁ፤ ስለዚህ ጠላቶቼን ስትበቀል እንዳይ አድርገኝ።
እነርሱንም ወደ እሳት እጨምራቸዋለሁ፤ ብርም በእሳት እንደሚጠራ አጠራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ ከዚያን በኋላ ወደ እኔ ይጸልያሉ፤ እኔም እመልስላቸዋለሁ። እኔ ‘ሕዝቤ’ ብዬ እጠራቸዋለሁ፤ እነርሱም ‘እግዚአብሔር አምላካችን’ ብለው ይጠሩኛል።”