መዝሙር 22:28 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሥልጣን ሁሉ የአንተ ነው፤ ሕዝቦችም ሁሉ ይገዙልሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መንግሥት የእግዚአብሔር ናትና፤ ሕዝቦችንም የሚገዛ እርሱ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የምድር ዳርቻዎች ሁሉ ያስቡ፥ ወደ ጌታም ይመለሱ፥ የአሕዛብ ነገዶች ሁሉ በፊቱ ይሰግዳሉ። |
የዘመኑ ፍጻሜ ሲደርስ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የተሠራበት ተራራ ከሌሎች ተራራዎች ሁሉ በልጦ ይታያል፤ ከኰረብቶችም ሁሉ እጅግ ከፍ ይላል፤ የብዙ መንግሥታት ሕዝቦች ወደ እርሱ ይጐርፋሉ።
ከወር መባቻ እስከ ሌላ የወር መባቻ በዓልና ከሰንበት እስከሚቀጥለው ሰንበት ሕዝብ ሁሉ በአዲሲቱ ኢየሩሳሌም ሊሰግዱልኝ ይመጣሉ”፤ ይህን የተናገርኩ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።
በልዩ ልዩ አገር የሚኖሩ ሕዝቦችና ልዩ ልዩ ቋንቋ የሚናገሩ ነገዶች ያገለግሉት ዘንድ ሥልጣን፥ ክብርና ንጉሥነት ተሰጠው፤ ግዛቱም የማይጠፋ ዘለዓለማዊ ነው፤ ለመንግሥቱም ፍጻሜ የለውም።
በምድራቸው ያሉትን ሐሰተኞች አማልክት ሁሉ በማጥፋቱ እግዚአብሔር በእነርሱ ዘንድ የተፈራ ይሆናል፤ በባሕር ጠረፍና በደሴቶች የሚኖሩ መንግሥታት ሁሉ በያሉበት ለእርሱ ይሰግዳሉ።
ሰባተኛውም መልአክ እምቢልታውን ነፋ፤ በሰማይም “የዓለም መንግሥት የጌታ የአምላካችንና የመሲሑ ሆናለች፤ እርሱ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይነግሣል፤” የሚሉ ታላላቅ ድምፆች ተሰሙ።