ምንጊዜም በማይፈርስ ድንጋጌ ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም መሥርቶአቸዋል።
ከዘላለም እስከ ዘላለም አጸናቸው፤ የማይሻርም ሕግ ደነገገላቸው።
ለዘለዓለም ዓለም አቆማቸው፥ ትእዛዝን ሰጠ፥ አያልፉትምም።
ለዘለዓለም አቆማቸው፤ ትእዛዝን ሰጣቸው፥ አላለፉምም።
ሰማያት በምን ዐይነት ሥርዓት እንደሚተዳደሩ ታውቃለህን? ይህንንስ ደንብ በምድር ላይ እንዲሠራ ለማድረግ ትችላለህን?
በሰማይ በእውነተኛነት እንደምትመሰክረው እንደ ጨረቃም የጸና ይሆናል።”
እግዚአብሔር ንጉሥ ነው፤ ግርማንና ኀይልን ተጐናጽፎአል፤ ምድርን በአንድ ስፍራ አጸናት፤ ከቶም አትናወጥም።
“በኖኅ ዘመን ‘ምድርን በውሃ መጥለቅለቅ እንደገና አላጠፋትም’ ብዬ ቃል እንደ ገባሁ እነሆ አሁንም ‘በአንቺ ላይ እንደገና አልቈጣም’ ብዬ ቃል እገባልሻለሁ፤ ከእንግዲህም ወዲህ ተግሣጽ አላደርስብሽም።
ቀጥሎም እግዚአብሔር እንዲህ አለ፦ “ለቀንና ለሌሊት መፈራረቅ፥ ለሰማይና ለምድር ቋሚ ሥርዓት የሰጠሁበትን ቃል ኪዳን ያልመሠረትሁ ከሆነ፥