እጅህን ከፍተህ የእያንዳንዱን ሕያው ፍጥረት ፍላጎት ታረካለህ።
አንተ እጅህን ትዘረጋለህ፤ የሕያዋን ፍጥረታትንም ሁሉ ፍላጎት ታረካለህ።
አንተ እጅህን ትከፍታለህ፥ ሕይወት ላለውም ሁሉ መልካምን ታጠግባለህ።
እንዲሁም ለአንተና ለእነዚህ ፍጥረቶች ሁሉ የሚበቃ ልዩ ልዩ ዐይነት ምግብ በመርከቡ ውስጥ አከማች።”
ዝናብ እንዲዘንብ የሚያደርግ ማነው? ጠፍና ባድማ የሆነውን መሬት ረስርሶ ምድሩንም ሣር እንዲያበቅል ያደረገው ማነው?
አንተ ምግብ ስትሰጣቸው እነርሱም ይመገባሉ፤ አንተ እጅህን ስትዘረጋ እነርሱም መልካም የሆነውን ነገር ሁሉ በልተው ይጠግባሉ።
እርሱ የተጠሙትን ያረካቸዋል፤ የተራቡትንም ብዙ መልካም ነገር በመስጠት ያጠግባቸዋል።
ለጽዮን ምግብዋን አበዛለሁ፤ ድኾችዋንም እስከሚጠግቡ አበላቸዋለሁ።
ለእንስሶች ምግብን ይሰጣል፤ ምግብ አጥተው የሚጮኹ የቊራ ጫጩቶችንም ይመግባል።