እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፥ በእስራኤልም ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው።
መዝሙር 141:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳኞቻቸው በገደል አለት ላይ በተጣሉ ጊዜ ሕዝቦቻቸው የእኔ ቃል እውነት መሆኑን ያረጋግጣሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሹማምንታቸው ከገደል አፋፍ ቍልቍል ይወረወራሉ፤ ቃሌ የምታረካ ናትና ይሰሟታል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለቆቻቸው በዓለት አጠገብ ተጣሉ፥ ጣፋጭ ናትና ቃሌን ይሰማሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እጅግ ተዋርጃለሁና ወደ ልመናዬ ተመልከት፤ በርትተውብኛልና ከከበቡኝ አድነኝ። |
እግዚአብሔር ከፍ ከፍ ያደረገው፥ በያዕቆብ አምላክ የተቀባው፥ በእስራኤልም ዘንድ መልካም ባለመዝሙር የሆነው፥ የእሴይ ልጅ የዳዊት የመጨረሻ ቃሉ ይህ ነው።
እነዚህ ሁሉ ለጦርነት ዝግጁ የሆኑ ወታደሮች ዳዊትን በመላው እስራኤል ላይ ለማንገሥ ቊርጥ ውሳኔ አድርገው ወደ ኬብሮን ሄዱ፤ የቀሩትም እስራኤላውያን በዚሁ ዓላማ በአንድነት ተስማምተው ነበር፤
ከዚያም በኋላ ለመላው የእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ሲል አስታወቀ፥ “እናንተ ከተስማማችሁበትና የአምላካችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ፥ የቀሩት የአገራችን ሰዎች፥ ካህናትና ሌዋውያን ወደሚኖሩባቸው ታናናሽ ከተማዎች መልእክተኞች ልከን ወደዚህ መጥተው ከእኛ ጋር እንዲሰበሰቡ እንንገራቸው፤
ሌሎች ዐሥር ሺህ ወታደሮችንም ማረኩ፤ እስረኞቹንም ሴላዕ ተብላ በምትጠራው ከተማ አጠገብ በሚገኘው ገደል አፋፍ ላይ አውጥተው ጣሉአቸው፤ ሁሉም ከገደሉ በታች በሚገኙ አለቶች ላይ ተፈጥፍጠው ሞቱ።