Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




1 ዜና መዋዕል 13:2 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ከዚያም በኋላ ለመላው የእስራኤል ሕዝብ እንዲህ ሲል አስታወቀ፥ “እናንተ ከተስማማችሁበትና የአምላካችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ፥ የቀሩት የአገራችን ሰዎች፥ ካህናትና ሌዋውያን ወደሚኖሩባቸው ታናናሽ ከተማዎች መልእክተኞች ልከን ወደዚህ መጥተው ከእኛ ጋር እንዲሰበሰቡ እንንገራቸው፤

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ከዚያም ለመላው የእስራኤል ማኅበር እንዲህ አለ፤ “እንግዲህ ነገሩ መልካም መስሎ ከታያችሁና የአምላካችን የእግዚአብሔር ፈቃድ ከሆነ፣ በእስራኤል ግዛት ሁሉ ለሚኖሩ በሩቅም ሆነ በቅርብ ላሉት ለቀሩት ወንድሞቻችን እንዲሁም በየራሳቸው ከተሞችና መሰማሪያዎች የሚኖሩ ካህናትና ሌዋውያን መጥተው ከእኛ ጋራ እንዲሰባሰቡ እንላክባቸው።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ዳዊትም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ እንዲህ አላቸው፦ “መልካም መስሎ ቢታያችሁ፥ የጌታም የአምላካችን ፈቃድ ቢሆን፥ በእስራኤል አገር ሁሉ ለቀሩት ወንድሞቻችን በከተሞቻቸውና በመሰማሪያዎቻቸውም ለተቀመጡት ካህናትና ሌዋውያን ወደ እኛ እንዲሰበሰቡ እንላክባቸው፤

Ver Capítulo Copiar

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ዳዊ​ትም የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ጉባኤ ሁሉ፥ “መል​ካም መስሎ የታ​ያ​ችሁ እንደ ሆነ፥ አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፈቅዶ እንደ ሆነ፥ በእ​ስ​ራ​ኤል ሀገር ሁሉ ለቀ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን በከ​ተ​ሞ​ቻ​ቸ​ውና በመ​ሰ​ማ​ሪ​ያ​ዎ​ቻ​ቸው ለሚ​ቀ​መጡ ካህ​ና​ትና ሌዋ​ው​ያን ወደ እኛ ይሰ​በ​ሰቡ ዘንድ እን​ላክ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 ዳዊትም የእስራኤልን ጉባኤ ሁሉ “መልካም መስሎ የታያችሁ እንደ ሆነ፥ ከአምላካችን ከእግዚአብሔርም ወጥቶ እንደ ሆነ፥ በእስራኤል አገር ሁሉ ለቀሩት ወንድሞቻችን በከተሞቻቸውና በመሰማርያዎቻቸውም ለሚቀመጡ ካህናትና ሌዋውያን ወደ እኛ ይሰበሰቡ ዘንድ እንላክ፤

Ver Capítulo Copiar




1 ዜና መዋዕል 13:2
16 Referencias Cruzadas  

ሽማግሌዎቹም “ዛሬ ለእነዚህ ሰዎች ታዛዥ ሆነህ ብታገለግላቸውና ለጥያቄአቸውም ተስማሚ የሆነ መልስ ብትሰጣቸው፥ እነርሱም ዘወትር በታማኝነት ያገለግሉሃል” ሲሉ መለሱለት።


በኢይዝራኤል በሸለቆው ይኖሩ የነበሩት እስራኤላውያን ሠራዊቱ እንደ ሸሸ፥ ሳኦልና ልጆቹም እንደ ሞቱ በሰሙ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ከተሞቻቸውን ያዙ።


ንጉሥ ዳዊት የሻለቅነትና የመቶ አለቅነት ማዕርግ ካላቸው የጦር አለቆች ጋር ተመካከረ፤


በሳኦል ዘመነ መንግሥት ችላ ብለነው የነበረውንም የእግዚአብሔርን የቃል ኪዳን ታቦት ሄደን እናመጣለን።”


በዚህ ዐይነት ብትሠራና ይህም የእግዚአብሔር ፈቃድ ቢሆን ራስህን በከንቱ አታደክምም፤ ሕዝቡም በቀላሉ ጉዳዩ እየተፈጸመለት ወደየቤቱ ይሄዳል።”


መልካም ምክርን ብትቀበል ሁሉ ነገር ይሳካልሃል፤ ምክርን ባትቀበል ግን ምንም ነገር አይሳካልህም።


የአሦር ንጉሥ ሕያው እግዚአብሔርን እንዲሰድብለት ከፍተኛ ባለሥልጣኑን ልኮአል፤ አምላክህ እግዚአብሔር ይህን ስድብ ሰምቶ ተሳዳቢውን ይቀጣ ይሆናል፤ ስለዚህ ከሕዝባችን መካከል በሕይወት ስለሚተርፉት እባክህ ወደ አምላክህ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ።”


ፍልስጥኤማውያን በጊልቦዓ ተራራ ከእስራኤላውያን ጋር ጦርነት ገጠሙ፤ ብዙ እስራኤላውያንም ሸሹ፤ ብዙዎችም ተገደሉ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos