መዝሙር 136:6 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምድርን በጥልቅ ውሃዎች ላይ መሠረተ፤ ፍቅሩ ዘለዓለማዊ ነው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምድርን በውሃ ላይ የዘረጋ፤ ምሕረቱ ለዘላለም ነውና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምድርን በውኃ ላይ ያጸናውን፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ባላስብሽ፥ ምላሴ በጕሮሮዬ ይጣበቅ፤ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን ባልወድድ። |
እግዚአብሔር ከምድር ክበብ በላይ ዙፋኑን ዘርግቶ መቀመጡን ሰማይን እንደ መጋረጃ መወጠሩንና፥ እንደ መኖሪያ ድንኳን መዘርጋቱን የምድርም ሕዝቦች እንደ ፌንጣ አነስተኞች መሆናቸውን።
ሰማይን የፈጠረና ከዳር እስከ ዳር የዘረጋው፥ ምድርንና በውስጥዋ የሚኖሩትን ሁሉ የሠራ፥ ሕይወትንና እስትንፋስንም የሰጣቸው፥ እግዚአብሔር አምላክ እንዲህ ይላል፦
በእናትህ ማሕፀን የፈጠረህ አዳኝህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሁሉን ነገር የፈጠርኩ፥ ሰማያትን ብቻዬን የዘረጋሁ፥ ምድርንም ብቻዬን ያነጠፍኩ፥ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።