መዝሙር 135:13 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ሆይ! ስምህ ዘወትር ሲታወጅ ይኖራል፤ ትውልድ ሁሉ ያስታውሱሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔር ሆይ፤ ስምህ ዘላለማዊ ነው፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ መታሰቢያህም ከትውልድ እስከ ትውልድ ይኖራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አቤቱ፥ ስምህ ለዘለዓለም ነው፥ ዝክርህም ለልጅ ልጅ ነው፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የኤርትራን ባሕር ፈጽሞ የከፈለ፤ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤ |
የንጉሡ ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑር፤ ዝናውም ፀሐይ በሚወጣበት ዘመን ሁሉ ይሰማ፤ ሕዝቦች ሁሉ በእርሱ የተባረኩ ይሁኑ፤ እርሱንም “የተባረከ ነው!” ይሉታል።
እግዚአብሔርም እንደገና ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ለእስራኤል ሕዝብ እንዲህ በላቸው፦ የአባቶቻችሁ የአብርሃም፥ የይስሐቅ፥ የያዕቆብ አምላክ እግዚአብሔር ወደ እናንተ ልኮኛል፤ ይህ የዘለዓለም ስሜ ነው፤ በዚህም ስም ከትውልድ እስከ ትውልድ እታወቃለሁ።