ብዙ የአሕዛብ መንግሥታትን ደመሰሰ፤ ኀያላን ነገሥታትንም ገደለ።
ብዙ ሕዝቦችን መታ፤ ኀያላን ነገሥታትንም ገደለ።
ብዙ አሕዛብን መታ፥ ብርቱዎችንም ነገሥታት ገደለ።
ከበኵራቸው ጋር ግብፅን የገደለ፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና፤
እስራኤላውያን ግን ድል ነሡአቸው፤ ከአርኖን ወንዝ አንሥቶ በስተሰሜን እስከ ዐሞናውያን ወሰን ማለትም እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ የሚገኘውን ግዛት ያዙ፤ ይሁን እንጂ የዐሞናውያን ወሰን በብርቱ የተጠበቀ በመሆኑ ወደዚያ አልገቡም።
ስለዚህ እስራኤላውያን ዖግን፥ ልጆቹን፥ ሕዝቡን ሁሉ አንድም ሳያስቀሩ ፈጅተው ምድሩን ወረሱ።