እግዚአብሔር ሆይ! የኀይልህ መግለጫ ከሆነችው ከቃል ኪዳን ታቦት ጋር ወደምታርፍበት ወደ ቤተ መቅደስ ግባ።
እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ፣ ከኀይልህ ታቦት ጋራ ወደ ማረፊያ ቦታህ ግባ።
አቤቱ፥ ወደ ዕረፍትህ ተነሥ፥ አንተና የመቅደስህ ታቦት።
እግዚአብሔር ይነሣ! ጠላቶቹም ይበተኑ! የሚጠሉትም ከፊቱ ይሽሹ!
የኀይሉና የክብሩ መታወቂያ ምልክት የነበረችውን የቃል ኪዳን ታቦት፥ ጠላቶች ማርከው እንዲወስዱአት አደረገ።