La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




መዝሙር 127:5 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እንደነዚህ ፍላጻዎች የሆኑ ብዙ ልጆች ያሉት ሰው የታደለ ነው፤ ከጠላቶቹ ጋር በፍርድ አደባባይ በሚከራከርበት ጊዜ ከቶ አይሸነፍም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ብፁዕ ነው፤ ኰረጆዎቹ በእነዚህ የተሞሉ ሰው፤ ከጠላቶቻቸው ጋራ በአደባባይ በሚሟገቱበት ጊዜ፣ አይዋረዱም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ከእነርሱ ዘንድ ምኞቱን የሚፈጽም ሰው የታደለ ነው፥ ጠላቶቻቸውን በአደባባይ በተናገሩ ጊዜ እርሱ አያፍርም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከጽ​ዮን ይባ​ር​ክህ፤ በሕ​ይ​ወ​ትህ ዘመን ሁሉ፥ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምን መል​ካ​ም​ነት ታያ​ለህ።

Ver Capítulo



መዝሙር 127:5
6 Referencias Cruzadas  

የኤፍሬምንም ልጆችና የልጅ ልጆች እስከሚያይ ድረስ ቈየ፤ ከምናሴ የተወለደውንም የማኪርንም ልጆች እንደ ልጆቹ አድርጎ ተቀበላቸው።


ሰባት ወንዶችና ሦስት ሴቶች ልጆችም ነበሩት።


ልጆቹም የኑሮ ዋስትና አያገኙም፤ በአደባባይም የሚከራከርላቸው ስለማያገኙ ጥቃት ይደርስባቸዋል።


እርሱ ጠላቶቼን ይበቀልልኛል፤ ሕዝቦችንም ከበታቼ አድርጎ ያስገዛልኛል።


ልጄ ሆይ! ጠቢብ ብትሆን ደስ ይለኛል፤ ለሚሰድበኝ ሁሉ የምሰጠውም መልስ ይኖረኛል።