“እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ባይሆን ጠላቶቻችን ባጠቁን ጊዜ
ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ከእኛ ጋራ ባይሆን ኖሮ፣
ጌታ ከእኛ ጋር ባይሆን ሰዎች በእኛ ላይ በተነሡ ጊዜ፥
ተራሮች ይከቧታል፥ ከዛሬ ጀምሮ ለዘለዓለም እግዚአብሔር ሕዝቡን ይመግባል።
ክፉ ሰዎች እንደ ውሻ ስብስብ ከበቡኝ፤ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩ።
እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶቼ እንዴት ብዙዎች ናቸው! ብዙዎችም በጠላትነት በእኔ ላይ ተነሥተዋል፤
ብዙ ሰዎች “እግዚአብሔር አያድነውም” እያሉ ስለ እኔ ይናገራሉ።
ክፉ ሰው በጻድቁ ላይ ይሸምቃል፤ ሊገድለውም ይፈልጋል።
ይህም ከእኔ ጋር የሆነው እግዚአብሔር፥ ቃሉን የማመሰግነውና የማከብረው አምላክ ነው።