መዝሙር 119:176 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደ ጠፋ በግ ተቅበዝብዤአለሁ፤ ነገር ግን ትእዛዞችህን ስላልረሳሁ፥ እኔን አገልጋይህን ፈልገኝ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ፤ ትእዛዞችህን አልረሳሁምና፣ ባሪያህን ፈልገው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንደ ጠፋ በግ ተቅበዘበዝሁ፥ ትእዛዛትህን አልረሳሁምና ባርያህን ፈልገው። |
እጄን ይዘህ ሳበኝ፤ አብረን እንሩጥ። ንጉሡ ወደ እልፍኙ አስገባኝ፤ በዚያም አብረን ደስ ይለናል፤ ፍቅርህ ከወይን ጠጅ ይልቅ ያስደስታል፤ ስለዚህ ቈነጃጅት ሁሉ እጅግ ያፈቅሩሃል።
ሁላችንም እንደ በጎች ባዝነን ነበር፤ ሁላችንም ወደ ራሳችን መንገድ ሄደን ነበር፤ ነገር ግን እግዚአብሔር የሁላችንንም በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
“የእስራኤል ሕዝብ በሐዘን እንዲህ ሲሉ ሰማኋቸው፤ ‘እግዚአብሔር ሆይ! እኛ እንዳልተገራ ወይፈን ነበርን፤ አንተ ግን መታዘዝን አስተማርከን፤ አንተ አምላካችን ስለ ሆንክ አሁንም ወደ አንተ ወደ አምላካችን መልሰን፤ እኛም እንመለሳለን።
“ሕዝቤ እንደ ጠፉ በጎች ሆነዋል፤ ጠባቂዎቻቸውም አሳቱአቸው፤ በተራራ ላይ ባዝነው እንዲቀሩም አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኰረብታ እንደሚባዝኑ በጎች ተንከራተቱ፤ ማደሪያቸውንም ረሱ።
“የጠፉትን እፈልጋለሁ፤ የባዘኑትን እመልሳለሁ፤ የተሰበሩትን እጠግናለሁ፤ ደካሞችን አበረታለሁ፤ እኔ ትክክለኛ እረኛ ስለ ሆንኩ በግፍ የሰቡትንና ብርቱዎች የሆኑትን አጠፋለሁ።
ሕዝቤ እኔን በሚገባ ካለማወቁ የተነሣ ጠፍቶአል፤ እናንተ እኔን ለማወቅ ስላልፈለጋችሁ እኔም ካህናት ሆናችሁ እንድታገለግሉኝ አልፈልጋችሁም፤ ሕጌንም ስላቃለላችሁና ስለ ረሳችሁ ልጆቻችሁ በእኔ ዘንድ የተረሱ ይሆናሉ።
በዚህ መንጋ ውስጥ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፤ እነርሱንም ማምጣት ይገባኛል፤ እነርሱ ድምፄን ይሰማሉ፤ አንድ መንጋም ይሆናሉ፤ እረኛውም አንድ ይሆናል።
አሁን ግን እግዚአብሔርን ዐውቃችኋል፤ ይልቁንም እግዚአብሔር እናንተን ዐውቋችኋል፤ ታዲያ፥ ወደ እነዚያ ወደ ደካሞችና ወደማይረቡት የዓለም ሥርዓቶች እንዴት ተመለሳችሁ? እንዴትስ እንደገና የእነርሱ ባሪያዎች ለመሆን ትፈልጋላችሁ?
መልካም ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከእግዚአብሔር ነው፤ ይህም የሚመጣው እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከብርሃን አባት ከእግዚአብሔር ነው።