በመሪዎች ከመመካት ይልቅ፥ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።
በገዦች ተስፋ ከማድረግ ይልቅ፣ በእግዚአብሔር መታመን ይሻላል።
በኃያላን ከመታመን ይልቅ በጌታ መጠለል ይሻላል።
ጐልማሳ መንገዱን በምን ያቀናል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።
ብዙ ፈረሶች፥ ሠረገሎችና ወታደሮች ባሉት ብርቱ በሆነው በግብጽ ሠራዊት ተማምነው ርዳታ ለማግኘት ወደ ግብጽ ለሚወርዱ ወዮላቸው! ነገር ግን የእስራኤልን ቅዱስ ርዳታ አይለምኑም፤ መመሪያውንም አይቀበሉም።
ከዚያ በኋላ አሦራውያን የሰው ባልሆነ ሰይፍ ይወድቃሉ።
በእጆቻችሁ በያዙአችሁ ጊዜ ተሰነጣጥቃችሁ ትከሻቸውን ወጋችሁ፤ በእናንተ ላይ በተደገፉ ጊዜ እናንተ ተሰብራችሁ ወገባቸው ተብረከረከ።
ሕዝቡ “እግዚአብሔርን መፍራት ስለ ተውን ንጉሥ አጥተናል፤ ንጉሥ ቢኖረንስ ምን ያደርግልናል?” ይላሉ።