እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ አድነን! እግዚአብሔር ሆይ! እባክህ ሁሉ ነገር የተሟላ እንዲሆን አድርግልን!
እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አድነን፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እባክህ አሳካልን።
አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አድን፥ አቤቱ፥ እባክህ፥ አሁን አቅና።
ሰውነቴ ወደ ምድር ተጣበቀች፤ እንደ ቃልህ ሕያው አድርገኝ።
አምላክ ሆይ! ንጉሡን ከጠላቶቹ እጅ አድነው፤ እኛም በምንጠራህ ጊዜ ስማን።
ከአንበሳ አፍ አድነኝ ከተዋጊ ጐሽ ቀንድም ጠብቀኝ።
የውሃ ሙላት እስከ አንገቴ ስለ ደረሰ፤ አምላክ ሆይ! አድነኝ!
እግዚአብሔር ሆይ! እኔ ግን ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ አንተ በመረጥከው ጊዜ ጸሎቴን መልሰህ፥ በዘለዓለማዊው ፍቅርህ ማዳንህን አረጋግጥልኝ።
እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! በረከትህ ከእኛ ጋር ይሁን፤ የምናደርገውንም ሁሉ አሳካልን።