እግዚአብሔር ከለላዬና መከላከያዬ ነው፤ አዳኜም እርሱ ነው።
እግዚአብሔር ብርታቴና ዝማሬዬ ነው፤ አዳኝ ሆነልኝ።
ኃይሌም ዝማሬዬም ጌታ ነው፥ እርሱም መድኃኒት ሆነልኝ።
እንደ ብልጥግና ሁሉ በምስክርህ መንገድ ደስ አለኝ።
እግዚአብሔር አለቴ፥ አምባዬና አዳኜ ነው፤ አምላኬ የምጠጋበት አለቴ ነው፤ እርሱ ጋሻዬና የመዳኔ ቀን፥ ጠንካራ መመኪያም ነው።
እግዚአብሔር ብርሃኔና ደኅንነቴ ስለ ሆነ ማንንም አልፈራም እግዚአብሔር የሕይወቴ ከለላ ስለ ሆነ የሚያስፈራኝ ማነው?
በእርግጥ እግዚአብሔር መድኃኒቴ ነው፤ በእርሱ ስለምተማመን የሚያስፈራኝ የለም፤ እግዚአብሔር አምላክ ኀይሌና ብርታቴ ነው፤ እርሱም መድኃኒቴ ሆኖአል።
እናንተ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከእግዚአብሔር በሚሰጣችሁ ዘለዓለማዊ ደኅንነት ትድናላችሁ፤ ለዘለዓለምም ኀፍረትና ውርደት ከቶ አይደርስባችሁም።