መዝሙር 117:1 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም መንግሥታት ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑት! ሕዝቦች ሁሉ አመስግኑት! አዲሱ መደበኛ ትርጒም አሕዛብ ሁላችሁ፤ እግዚአብሔርን አመስግኑት፤ ሕዝቦችም ሁሉ፤ ወድሱት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሃሌ ሉያ! አሕዛብ ሁላችሁ፥ ጌታን አመስግኑት፥ ሕዝቦችም በሙሉ አመስግኑት፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን አመስግኑ፥ ቸር ነውና፥ ምሕረቱ ለዘለዓለም ነውና። |
ጌታ ሆይ! አንተን የማይፈራና ስምህንም የማያከብር ማን ነው? አንተ ብቻ ቅዱስ ነህ፤ የእውነት ፍርድህ ስለ ተገለጠ፥ ሕዝቦች ሁሉ መጥተው በፊትህ ይሰግዳሉ።”
አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤