የሞት አደጋ ዙሪያዬን ከበበኝ፤ የመቃብር አስፈሪ ሁኔታ አሠቀቀኝ፤ በችግርና በሐዘን ተሸነፍኩ።
የሞት ወጥመድ ያዘኝ፤ የሲኦልም ጣር አገኘኝ፤ ጭንቅና ሐዘን አሸነፈኝ።
የሞት ገመዶች ወጠሩኝ፥ የሲኦልም ሕማም አገኘኝ፥ ጭንቀትንና መከራን አገኘሁ።
ጐበጥኩ፤ እጅግም እያጐነበስኩ ሄድኩ፤ ቀኑን ሙሉ በትካዜ አሳለፍኩ።
ልቡም በጣም ተጨንቆ በብርቱ ይጸልይ ነበር፤ ላቡም እንደ ደም ሆኖ ወደ መሬት ይንጠባጠብ ነበር።
ኢየሱስ ሰው ሆኖ በዚህ ምድር በኖረበት ጊዜ ከሞት ሊያድነው ወደሚችል አምላክ በታላቅ ጩኸትና በብዙ እንባ ጸሎትንና ልመናን አቀረበ፤ በትሕትና ራሱን ታዛዥ በማድረጉ እግዚአብሔር ጸሎቱን ሰማው።