እኛ ግን በሕይወት ያለነው ከአሁኑ ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም እናመሰግነዋለን። እግዚአብሔር ይመስገን!
ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘላለም፣ እግዚአብሔርን የምንባርክ እኛ ነን። እግዚአብሔር ይመስገን።
እኛ ሕያዋን ግን ከአሁን ጊዜ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ጌታን እንባርካለን። ሃሌ ሉያ።
አሁንም ለዘለዓለም ስሙ ይመስገን።
በየቀኑ አመሰግንሃለሁ፤ ለዘለዓለምም ስምህን አከብራለሁ።
እኔ ሁልጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ እርሱ የፈጠራቸው ሁሉ ቅዱስ ስሙን ለዘለዓለም ያወድሱ።
“ጥበብም ኀይልም የእርሱ ስለ ሆነ እግዚአብሔር ለዘለዓለም የተመሰገነ ይሁን!
በሰማይና በምድር፥ ከምድር በታችና በባሕር፥ በውስጣቸውም ፍጥረቶች ሁሉ “በዙፋኑ ላይ ለተቀመጠውና ለበጉም ምስጋና፥ ገናናነት፥ ክብርና ኀይል ለዘለዓለም እስከ ዘለዓለም ይሁን!” ሲሉ ሰማሁ።