እርሱ የተጠሙትን ያረካቸዋል፤ የተራቡትንም ብዙ መልካም ነገር በመስጠት ያጠግባቸዋል።
እርሱ የተጠማችውን ነፍስ አርክቷልና፤ የተራበችውንም ነፍስ በበጎ ነገር አጥግቧል።
የተጠማችን ነፍስ አጥግቦአልና፥ የተራበችን ነፍስ በበረከት ሞልቶአልና።
ካህን ሞዓብም ተስፋዬ ነው፥ በኤዶምያስ ላይም ጫማዬን እዘረጋለሁ፤ ፍልስጥኤምም ይገዙልኛል።
ለጽዮን ምግብዋን አበዛለሁ፤ ድኾችዋንም እስከሚጠግቡ አበላቸዋለሁ።
ለተጨቈኑት ፍትሕን ይሰጣል፤ ለተራቡ ምግብን ይሰጣል። እስረኞችን ነጻ ያወጣል።
ድኾች እስኪጠግቡ ይበላሉ፤ እግዚአብሔርን የሚሹት ያመሰግኑታል፤ ልባቸው በሕይወት ዘመናቸው ሁሉ ይደሰታል።
የአንበሳ ደቦሎች ያጣሉ፤ ይራባሉም፤ እግዚአብሔርን የሚፈልጉት ግን ምንም አይጐድልባቸውም፤ መልካም ነገርም አያጡም።
ልጆቼ ሆይ! ኑ አድምጡኝ፤ እኔም እግዚአብሔርን መፍራት አስተምራችኋለሁ።
ካህናቱን በምድሪቱ በረከት አጠግባቸዋለሁ፤ ለሕዝቤም ቸርነቴን አትረፈርፍላቸዋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
የደከሙትን ሁሉ ኀይላቸው እንዲታደስ አደርጋለሁ፤ በረሀብ ዝለው የነበሩትንም ምግብ በመስጠት አጠግባቸዋለሁ፤
ጽድቅን የሚራቡና የሚጠሙ ስለሚጠግቡ የተባረኩ ናቸው።
የተራቡትን በመልካም ነገር አጥግቦአቸዋል፤ ሀብታሞችን ግን ባዶ እጃቸውን ሰዶአቸዋል፤