እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አድነን! ከመንግሥታት መካከል መልሰህ ወደ አገራችን አግባን፤ በዚያን ጊዜ እናመሰግንሃለን፤ ቅዱስ ስምህንም እናከብራለን።
መዝሙር 107:3 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከባዕድም አገር መልሶ አምጥቶአችኋል፤ ከምሥራቅና ከምዕራብ፥ ከሰሜንና ከደቡብ ሰብስቦአችኋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ፣ ከየአገሩ የሰበሰባቸው እንዲህ ይናገሩ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከምሥራቅና ከምዕራብ፥ ከሰሜንና ከባሕር፥ ከየአገሩ ሰበሰባቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አቤቱ፥ በአሕዛብ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በወገኖችም መካከል እዘምርልሃለሁ፤ |
እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ! አድነን! ከመንግሥታት መካከል መልሰህ ወደ አገራችን አግባን፤ በዚያን ጊዜ እናመሰግንሃለን፤ ቅዱስ ስምህንም እናከብራለን።
የተበተኑትን እስራኤላውያንን የሚሰበስበው ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ከተሰበሰቡት ሌላ ሌሎችንም ወገኖች ወደ እነርሱ ሰብስቤ አመጣቸዋለሁ።”
በእርግጥ እላችኋለሁ ታገኙኛላችሁ፤ እኔም ወደ ምድራችሁ እመልሳችኋለሁ፤ እናንተን ከበተንኩበት ከየትኛውም አገርና ከየትኛውም ስፍራ ሁሉ እሰበስባችኋለሁ፤ እኔ እናንተን ነቅዬ እንድትሰደዱ ከማድረጌ በፊት ወደ ነበራችሁበት ምድር መልሼ አመጣችኋለሁ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።”
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “ሕዝቦች ሆይ! አድምጡኝ፤ በሩቅ ጠረፎችም ቃሌን ዐውጁ፤ እኔ ሕዝቤን በትኜ ነበር፤ አሁን ግን እሰበስባቸዋለሁ፤ እረኛ መንጋውን እንደሚጠብቅም እጠብቃቸዋለሁ።
“እኔ ከሰሜን አመጣቸዋለሁ፤ ከምድር ዳርቻም እሰበስባቸዋለሁ፤ ዕውሮች፤ አንካሶች፥ ነፍሰጡሮችና በምጥ የተያዙ ሴቶች ሁሉ ከእነርሱ ጋር አብረው ይመጣሉ፤ ታላቅ ሕዝብ ሆነው ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፤
አዲስ መዝሙርም እንዲህ እያሉ ዘመሩ፦ “በደምህ ከየነገዱ፥ ከየቋንቋው፥ ከየወገኑ፥ ከየሕዝቡ ሰዎችን ለእግዚአብሔር ለመዋጀት፥ አንተ ስለ ታረድህ የብራናውን ጥቅል መጽሐፍ ለመውሰድና ማኅተሞቹን ለመክፈት የተገባህ ሆነሃል፤