በጥጃ አምሳል ለራሳቸው ጣዖትን ሠርተው፥ ‘ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን አምላክ ይህ ነው!’ አሉ፤ በአንተ ላይም ከፍተኛ የስድብን ቃል እንኳ ተናገሩ፤
መዝሙር 106:19 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በኮሬብ ሳሉ የወርቅ ጥጃ ሠሩ፤ ለዚያም ጣዖት ሰገዱ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በኮሬብ ጥጃ ሠሩ፤ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በኮሬብም ጥጃን ሠሩ፥ ቀልጦ ለተሠራ ምስልም ሰገዱ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በተጨነቁም ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኹ፥ ከመከራቸውም አዳናቸው። |
በጥጃ አምሳል ለራሳቸው ጣዖትን ሠርተው፥ ‘ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን አምላክ ይህ ነው!’ አሉ፤ በአንተ ላይም ከፍተኛ የስድብን ቃል እንኳ ተናገሩ፤
ሕዝቡ ሙሴ ከተራራው ሳይወርድ እዚያ ብዙ እንደ ዘገየ ባዩ ጊዜ በአንድነት በመሰብሰብ አሮንን ከበው “ያ ከግብጽ ምድር መርቶ ያወጣን ሙሴ ምን እንደ ደረሰበት አናውቅም፤ ስለዚህ በፊት በፊታችን እየሄዱ የሚመሩን አማልክትን ሥራልን” አሉት።
“ሰዎች ሊበሉና ሊጠጡ ተቀመጡ፤ ከመጠን በላይ ሊፈነጥዙ ተነሡ” ተብሎ ስለ እነርሱ እንደ ተጻፈው፥ እነርሱ ጣዖትን እንዳመለኩ እናንተም እንደእነርሱ ጣዖትን አታምልኩ።
ያንንም በጥጃ አምሳል አቅልጣችሁ የሠራችሁትን በኃጢአት የተሞላ አጸያፊ ምስል አንሥቼ እሳት ውስጥ ጣልኩት፤ እርሱንም ሰባብሬ እንደ ትቢያ አደቀቅሁት፤ ትቢያውንም ከተራራው በሚወርደው ውሃ ውስጥ ጨመርኩት።