መዝሙር 104:35 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኃጢአተኞች ከምድር ላይ ይጥፉ! ግፍ አድራጊዎችም ይደምሰሱ! ነፍሴ ሆይ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! እግዚአብሔርን አመስግኚ! አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኃጥኣን ከምድር ገጽ ይጥፉ፤ ዐመፀኞች ከእንግዲህ አይገኙ። ነፍሴ ሆይ፤ እግዚአብሔርን ባርኪ። ሃሌ ሉያ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኀጥኣን ከምድር ይጥፉ፥ ዓመፀኞች ከእንግዲህ አይገኙ። ነፍሴ ሆይ፥ ጌታን ባርኪ። ሃሌ ሉያ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የምድራቸውንም ፍሬ ሁሉ በላ የተግባራቸውን ሁሉ መጀመሪያ በላ፥ |
በቊጣህ አጥፋቸው፤ ፈጽመህም ደምስሳቸው፤ በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር እስራኤልን እንደሚያስተዳድርና ግዛቱም በምድር ሁሉ እንደ ተንሰራፋ፥ ሰው ሁሉ ያውቃል።
እነሆ የእግዚአብሔር ቀን ቀርቦአል፤ የእግዚአብሔር ቊጣና መዓት የሚፈጸምበት ያ ቀን እጅግ አስፈሪ ነው፤ በዚያን ጊዜ በእርስዋ የሚኖረው ኃጢአተኛ ሕዝብ ስለሚደመሰስ ምድሪቱ ባድማ ትሆናለች።
እግዚአብሔር ሆይ! ጠላቶችህን ሁሉ በዚህ ዐይነት አጥፋ፤ ወዳጆችህ ግን እንደ ንጋት ፀሐይ ይድመቁ። ከዚህ በኋላ በምድሪቱ ላይ አርባ ዓመት ሙሉ ሰላም ሆነ።