በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ በሕይወትም እስካለሁ ድረስ ለአምላኬ የምስጋና መዝሙር አቀርባለሁ።
በሕይወት ሳለሁ ለእግዚአብሔር እዘምራለሁ፤ ቆሜ እስከ ሄድሁ ድረስም አምላኬን እወድሳለሁ።
በሕይወቴ ሳለሁ ለጌታ እቀኛለሁ፥ ለአምላኬም በምኖርበት ዘመን ሁሉ እዘምራለሁ።
ወይናቸውንና በለሳቸውን መታ፥ የሀገራቸውንም ዛፍ ሁሉ ሰበረ።
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በምኖርበት ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ።
በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አመሰግንሃለሁ፤ ለጸሎትም እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ።
ሰው መልካም ምግብ በልቶ እንደሚጠግብ ነፍሴ በአንተ ትረካለች፤ ስለዚህ የምስጋና መዝሙር በደስታ እዘምርልሃለሁ።
በመኝታዬም ሆኜ አስታውስሃለሁ፤ ሌሊቱንም ሁሉ የአንተን ነገር አስባለሁ።
እኔ ግን ስለ ያዕቆብ አምላክ ከመናገር ስለ ክብሩም ከመዘመር ከቶ አልቈጠብም።