ምሳሌ 9:8 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ትዕቢተኛን ሰው ብታርመው ይጠላሃል፤ ጠቢብን ሰው ብታርመው ግን ይወድሃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፌዘኛን አትዝለፈው፤ ይጠላሃል፤ ጠቢብን ገሥጸው፤ ይወድድሃል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፌዘኛን አትገሥጽ እንዳይጠላህ፥ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሰነፎችን አትገሥጽ እንዳይጠሉህ፥ ጠቢብን ገሥጽ ይወድድህማል። |
አክዓብም “የይምላ ልጅ የሆነ ሚክያስ የተባለ ሌላ ነቢይም አለ፤ ነገር ግን እኔ እርሱን አልወደውም፤ እርሱ ምን ጊዜም ቢሆን ስለ እኔ ክፉ እንጂ መልካም የትንቢት ቃል አይናገርም!” ሲል መለሰለት። ኢዮሣፍጥም “ይህን ማለት አይገባህም!” አለው።
ደግ ሰው በቅንነት መንፈስ ሊቀጣኝና ሊገሥጸኝ ይችላል፤ ከክፉ ሰዎች ግን ክብርን እንኳ አልቀበልም፤ ዘወትርም ክፉ ሥራቸውን በመቃወም እጸልያለሁ።
የተቀደሰውን ነገር ለውሾች አትስጡ፤ ዕንቋችሁንም በዐሣማዎች ፊት አትጣሉ፤ ዐሣማዎቹ ዕንቋችሁን በእግራቸው ይረግጡታል፤ ውሾቹም ተመልሰው ይነክሱአችኋል።