ምሳሌ 8:31 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ በፈጠረው ዓለም ደስ ይለኛል፤ በሰው ዘርም ሐሤት አደርጋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የርሱ በሆነው መላው ዓለም ሐሤት እያደረግሁ፣ በሰው ልጆች ደስ እሰኝ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደስታዬም በምድሩ ተድላዬም በሰው ልጆች ነበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ዓለምንም ፈጥሮ በፈጸመና ደስ ባለው ጊዜ፥ ደስታዬ በሰው ልጆች መካከል ነበር። |
እነሆ፥ ጊዜው ከአይሁድ ፋሲካ በዓል በፊት ነበር፤ ኢየሱስ ይህን ዓለም ትቶ ወደ አብ የሚሄድበት ሰዓት መድረሱን ዐወቀ። በዚህ በዓለም ያሉትን የራሱን ወገኖች ወዶአቸው ነበር፤ እስከ መጨረሻም ወደዳቸው።
እናንተ የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁ፤ እርሱ ምንም እንኳ ሀብታም ቢሆን በእርሱ ድኻ መሆን እናንተ ሀብታሞች እንድትሆኑ ስለ እናንተ ብሎ ድኻ ሆነ።