እነርሱ ከአመንዝራ ሴት እንድትርቅና ከሌላ ሰው ሚስት አሳሳች ቃል እንድትጠበቅ ያደርጉሃል።
ከአመንዝራ ሴት፣ በአንደበቷም ከምታታልል ባዕድ ሴት ይጠብቁሃል።
ከአምንዝራ ሴት ትጠብቅህ ዘንድ፥ ቃሏን ካለዘበች ከሌላይቱ ሴት።
ከባዕድና ከክፉ ሴት ዋዛ ነገርንም ከምታመጣብህ ትጠብቅህ ዘንድ።
እንግዲህ እኔ የምልህን ብትሰማ በልዝብ አነጋገር ከምታጠምድ ከአመንዝራ ሴት ማምለጥ ትችላለህ።
የአመንዝራ ሴት አፍ እንደ ጥልቅ ጒድጓድ ነው። እግዚአብሔር የጠላቸው ሰዎችም ተይዘው ይወድቁበታል።
ልጄ ሆይ! በአመንዝራይቱ ሴት ለምን ትማረካለህ? ለምንስ ከሌላው ሰው ሚስት ጋር ትባልጋለህ?
የአመንዝራ ሴት ከንፈር የማር ወለላ የሚያንጠባጥብ ይመስላል፤ ንግግርዋም ከዘይት ይልቅ የለዘበ ነው።
ከመጥፎ ሴት እንድትርቅና ከሌላ ሰው ሚስት አሳሳች ቃል እንድትጠበቅ ይረዱሃል።
በሚማርኩ ቃሎችዋ አግባባችው፤ በለዘበ አነጋገርዋም አታለለችው።
ጥበብን እንደ እኅትህ፥ ማስተዋልንም እንደ ቅርብ ወዳጅህ አድርገህ ቊጠራቸው።
ከዕለታት አንድ ቀን በቤቴ መስኮት ወደ ውጪ እመለከት ነበር፤