ምሳሌ 7:23 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፍላጻም ሆድ ዕቃውን እንደሚወጋው ዐይነት ሆነ፤ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ ወፍ መሰለ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕይወቱ በአደጋ ላይ ለመውደቅ መቃረቡን አላወቀም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ፍላጻ ጕበቱን እስኪወጋው ድረስ፣ ሕይወቱን እንደሚያሳጣው ሳያውቅ፣ በርራ ወደ ወጥመድ እንደምትገባ ወፍ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወፍ ወደ ወጥመድ እንደሚጣደፍ፥ ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሆን ሳያውቅ፥ ፍላጻ ጉበቱን እስኪሰነጥቀው ድረስ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ወጥመድ እንደሚቸኩል ዎፍ፥ ሳያውቅም ለነፍሱ ጥፋት እንደሚሮጥ። |
ከሞት ይልቅ የመረረ ሌላም ነገር አገኘሁ፤ ይኸውም የሴት ወጥመድነት ነው፤ ሴት እንደ መረብ በሆነ ፍቅርዋ ወንዶችን ታጠምዳለች፤ እንደ እግር ብረት በሆኑ ክንዶችዋም ተጠምጥማ ለመያዝ ትፈልጋለች፤ እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰው ብቻ ከእርስዋ ሸሽቶ ማምለጥ ይችላል፤ ኃጢአተኛውን ግን አጥምዳ ትይዘዋለች።
ይሁን እንጂ እያንዳንዱ ሰው ይህ መጥፎ ዕድል መቼ እንደሚገጥመው አያውቅም፤ ወፍ በራ በወጥመድ ውስጥ እንደምትገባ፥ ዓሣም በመጥፎ አጋጣሚ በመረብ እንደሚያዝ እንዲሁም የሰው ልጅ ሁሉ ሳያስበው ድንገት በሚደርስበት በክፉ አጋጣሚ ይጠመዳል።