ምሳሌ 7:22 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሬ ወደሚታረድበት ስፍራ እንደሚነዳ፥ አጋዘንም ቸኲሎ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ፥ ወዲያውኑ እርስዋን ተከትሎ ሄደ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ለዕርድ እንደሚነዳ በሬ፣ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ አጋዘን፣ ሳያንገራግር ተከተላት፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱ እንዲህ ስቶ ይከተላታል፥ በሬ ለመታረድ እንደሚነዳ፥ አጋዘን ቸኩሎ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርሱ አንገቱን ደፍቶ ይከተላታል፥ ለመታረድ እንደሚነዳ በሬ፥ ወደ እስራት እንደሚሄድ ውሻ፥ ሆዱ እንደ ተወጋ ዋሊያ፥ |
ፍላጻም ሆድ ዕቃውን እንደሚወጋው ዐይነት ሆነ፤ ወደ ወጥመድ እንደሚገባ ወፍ መሰለ፤ ይህ ሁሉ ሲሆን ሕይወቱ በአደጋ ላይ ለመውደቅ መቃረቡን አላወቀም።
ከከተማው ውጪ ያለው የድያ ቤተ መቅደስ ካህን ኮርማዎችንና የአበባ ጒንጒኖችን ወደ ከተማው በር አምጥቶ ከሕዝቡ ጋር በመተባበር ለጳውሎስና ለበርናባስ መሥዋዕት ሊያቀርብላቸው ፈለገ።