ከዚህ በኋላ እህላቸውን ከስልቾቻቸው ባራገፉ ጊዜ በየስልቻዎቻቸው ውስጥ ገንዘባቸውን እንደ ተቋጠረ አገኙ፤ እነርሱና አባታቸው የተመለሰውን ገንዘብ ባዩ ጊዜ እጅግ ፈሩ።
ምሳሌ 7:20 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ብዙ ገንዘብ ይዞ ስለ ሄደ እስከ ሁለት ሳምንት አይመለስም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በገንዘብ የተሞላ ቦርሳ ወስዷል፤ ጨረቃዋ ሙሉ እስክትሆን አይመለስም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በእጁም የብር ከረጢት ወስዶአል፥ ሙሉ ጨረቃ በሆነች ጊዜ ወደ ቤቱ ይመለሳል።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በእጁም የወርቅ ከረጢት ይዞአል፤ ወደ ቤቱ ቢመለስም ከብዙ ጊዜ በኋላ ነው።” |
ከዚህ በኋላ እህላቸውን ከስልቾቻቸው ባራገፉ ጊዜ በየስልቻዎቻቸው ውስጥ ገንዘባቸውን እንደ ተቋጠረ አገኙ፤ እነርሱና አባታቸው የተመለሰውን ገንዘብ ባዩ ጊዜ እጅግ ፈሩ።
አሁን እኔ ለአምላኬ ለእግዚአብሔር ስም ቤተ መቅደስን ለመሥራት በመዘጋጀት ላይ ነኝ፤ ይህም ቤተ መቅደስ እኔና ሕዝቤ በእግዚአብሔር ፊት ጣፋጭ ሽታ ያለውን ዕጣን የምናጥንበት የተቀደሰውን ኅብስት ሳናቋርጥ ለእግዚአብሔር የምናቀርብበት፥ በየቀኑ ጠዋትና ማታ፥ እንዲሁም በሰንበቶች፥ በወር መባቻዎችና በሌሎችም በተቀደሱ በዓላት እግዚአብሔር አምላካችንን ለማክበር የሚቃጠለውን መሥዋዕት የምናቀርብበት የተቀደሰ ስፍራ ይሆናል፤ የእስራኤል ሕዝብ ይህን ለዘለዓለም እንዲያደርጉ እግዚአብሔር አዞአል።
ባልዋም ሳያውቅ ከሌላ ወንድ ጋር በመተኛት ምንም ሳይታወቅባት ራስዋን አርክሳ ይሆናል፤ እጅ ከፍንጅም ባለመያዝዋ በእርስዋ ላይ መስካሪ አይኖርም፤